ሰቆቃወ ድንግል
1 ደቂቃ
ብክዩ ኅዙናን ሐልየክሙ ስደታ
# ብክዩ ኅዙናን ሐልየክሙ ስደታ
ብክዩ ኅዙናን ሐልየክሙ ስደታ ፣
ወላህዉ ፍሡሓን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ ፣
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕታ፤
ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ ፤
ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኲሉ ፍኖታ ፡፡
የድንግል ማርያምን ስደቷን አስባችሁ የምታዝኑ ፤ የቅንነቷንም ብዛት አስባችሁ የምትደሰቱ ሁሉ ፈጽማችሁ አልቅሱ ፤ የአባቷ የያዕቆብ (የዳዊት) አገር የምትሆን ኤፍራታን አጥታ ብቻዋን እንደ ወፍ እየዞረች ትጮኻለችና የሕፃናት ደምም በመንገዷ ሁሉ ይፈስሳል።
---
*የተጻፈበት ቀን: ሰኞ 4 ኦገስት 2025 ከሰዓት 7:59:42*