← ወደ ዋናው ገጽ
መረጃ
1 ደቂቃ

ገና ማለት ምን ማለት ነው?


# ገና ማለት ምን ማለት ነው?


ገና የሚለው ቃል ከጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ የተወረሰ ቃል እንደሆነ እና ትርጉሙም ልደት ማለት እንደሆነ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት መምህራን ይገልጻሉ። መጽሐፍት ላይ ስለ ልደት በዓል ከተጻፉት መካከል በጥቂቱ እናካፍላችሁ። እንዲህ ይላል፥ በትንቢተ ነቢያት የተነገረለት የሰውን ልጆች በጥንተ ተፈጥሮ የፈጠረ የእግዚአብሔር ልጅ ሰውን ለማዳን ሰው ሆኖ የተወለደበት ዕለት ነው። በዓለ ልደት በየዓመቱ የሚከበረው ታህሳስ 29 ቀን ነው።


---

*የተጻፈበት ቀን: 2025 ኦገስት 19, ማክሰኞ 1:53:47 ከሰዓት*


ይህን ጽሑፍ ያጋሩ