ማህሌተ ጽጌ
1 ደቂቃ
ለምንት ሊተ ኢትበሊ
# ለምንት ሊተ ኢትበሊ
ለምንት ሊተ ኢትበሊ እምአፈ ኃጥእ ውዳሴ። ይበቊዐኒ ዘብየ እመአፈ ጻድቃን ቅዳሴ። ጽጌ መድኀኒት ማርያም ዘሠረጽኪ እም ሥርወ እሴ። እመ ተወከፍኪ ኪያየ አባሴ ተአምረኪ የአኵት ብናሴ።
ድንግል ሆይ " ከኃጢአተኛ አፍ ምስጋና ለምኔ ፤ ከጻድቃን አፍ የሚቀርብልኝ ምስጋና ይበቃኛል " አትበዪ ፤ ከዕሤይ ሥር የበቀልሽ የመድኀኒት አበባ ማርያም ሆይ ፤ እኔን በደለኛውን ብትቀበዪ ተአምርሽን ጨረቃ ያመሰግናል።
ማሕሌት ዘጽጌ
---
*የተጻፈበት ቀን: 2025 ኦገስት 25, ሰኞ 11:32:48 ጥዋት*